የቴክሳስ አስተማሪ የሆነችው ሪታ ፒርሰን፣ በ61 ዓመቷ በድንገት ከመሞቷ ከጥቂት ወራት በፊት ለTED Talk በሰጠችው እና አንድ የስራ ባልደረባዋ “ልጆቹን እንድወድ ክፍያ አይከፍሉኝም” ስትላት አስታወሰች። የእሷ ምላሽ፡- "ልጆች ከማይወዷቸው ሰዎች አይማሩም።"
አወንታዊ የአስተማሪ እና የተማሪ ግንኙነቶች የተማሪዎችን አካዴሚክ ስኬት እንደሚያሳድጉ ብዙ ጊዜ እናውቃለን። ይህ የሆነበት ምክንያት ተማሪዎች ከሚያምኗቸው ሰው ጋር አደጋን ለመጋፈጥ ደህንነት ስለሚሰማቸው እና ምርጥ ስራቸውን ለመስራት ስለሚነሳሱ እንደሆነ ሁልጊዜ እንገምታለን። በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የታተመ ጥናት፣ ነገር ግን፣ ግኑኝነቶች በጣም ጠንካራ በሆኑባቸው የመማሪያ ክፍሎች ውስጥ ለከፍተኛ የፈተና ውጤቶች እና ጂፒኤኤስ (GPAs) የተለየ ማብራሪያን ይዳስሳል፡- እነዚህ ተማሪዎች የበለጠ እየተማሩ ያሉት ይበልጥ ውጤታማ በሆነ መንገድ ስለሚማሩ ነው? ማለትም፡- አወንታዊ የአስተማሪ እና የተማሪ ግንኙነቶች በእርግጥ አስተማሪዎች የሚያስተምሩበትን መንገድ ይለውጣሉ? መልሱ “አዎ” የሚል ሆኖ ተገኝቷል። ይህ የመጀመሪያ ምርምር አወንታዊ የአስተማሪ እና የተማሪ ግንኙነት በራሳቸው አስተማሪዎች ላይ የሚያሳድሩትን እውነተኛ ተፅእኖ ከሚመረምሩት ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው። ይህ በቅርቡ በ Learning and Instruction በሚባለው ጆርናል ላይ የታተመው ጥናት በሚዙሪ ከ4-10ኛ ክፍል ለሚያስተምሩ መምህራን ከሁለት የትምህርት ዓመታት ከተሰበሰበ የግምገማ መረጃ ላይ ያተኮረ ነው። ተመራማሪዎቹ እንደሚከተለው ይደመድማሉ፡- አዎንታዊ የአስተማሪ እና የተማሪ ግንኙነት የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን በዚህ ጥናት የተፈተሹትን ሶስት ውስብስብ የማስተማር ልምዶችን በብቃት እንዲተገብሩ ያደርጋቸዋል፡- በይዘቱ ውስጥ የግንዛቤ ተሳትፎ፣ ችግር መፍታት እና በጥልቀት ማሰብ እና ማገናዘብ እና የመመሪያ ክትትል… ፣ መምህራን የማረጋገጥ፣ የመከታተል፣ የማሳለጥ፣ ለተማሪዎች የበለጠ ገንቢ ግብረመልስ የመስጠት፣ በተማሪዎቻቸው ችሎታ ላይ የበለጠ እምነት እንዲኖራቸው እና በጥልቀት ለማሰብ እና ለማገናዘብ የተሻሉ የስካፎልዲንግ ስልቶችን የመጠቀም ዕድላቸው ሰፊ ነው። ተመራማሪዎቹ በተጨማሪም "የተፅዕኖ አቅጣጫን" መመርመር ችለዋል፣ ይህም ማለት አወንታዊው የአስተማሪ እና የተማሪ ግንኙነቶች ከፍተኛ ጥራት ያለው ትምህርት እንደሚያመላክቱ እና እንደሚቀድሙ ማሳየት ችለዋል። የመምህሩ የዓመታት ልምድ ምንም ይሁን ምን፣ በትምህርት ቤቱ የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸው ተማሪዎች መቶኛ፣ እና በትምህርት ቤት ደረጃ በስቴት ፈተናዎች ላይ ያለው የብቃት ደረጃ ይህ እውነት ነበር። አሁን ለምን ይህንን አነሳለሁ? ምክንያቱም ወደ አዲስ የትምህርት ዘመን እየሄድን ነው፣ እና በመጀመሪያዎቹ ሳምንታት በግንኙነቶች ላይ ለመሳተፍ የተወሰነ ጊዜ ብንወስድ ጥሩ ይሆናል። “ይህን መጠይቅ ሙላ፣ ወደ ትምህርት ቤት ምሽት ተመለስ” የሚለውን የተለመደ አይነት መስተጋብር ማለቴ አይደለም፡- መምህራን ተማሪዎቻቸውን ጠለቅ ብለው ለማወቅ የሚፈጀውን ጊዜ ቅድሚያ መስጠት እና ኢንቨስት ማድረግ ማለቴ ነው፣ እንዲሁም በተቃራኒው። ይህ ኢንቨስትመንት ለረጅም ጊዜ ዓመቱን ሙሉ ትርፍ ይከፍላል። ባለፈው ኦገስት(August)፣ ይህ ምን ሊመስል እንደሚችል ጽፌ ነበር። በወቅቱ እኔ በተማሪዎችላይ ስላለው ተጽእኖ እያሰብኩ ነበር፣ ነገር ግን ይህ የቅርብ ጊዜ ጥናት አሁን በአስተማሪዎች ላይም ያለውን ተጽእኖ ግምት ውስጥ ያስገባኛል። ከአንድ ሚሊዮን ዓመታት በፊት አስተማሪ በነበርኩበት ወቅት፣ የተለምዷዊ ጥበብ መምህራን በተለይ በመጀመሪያዎቹ የትምህርት ሳምንታት ጥብቅ መሆን አለባቸው የሚል እምነት ነበረው። ህጉን አስቀምጠው። በአንተ ቁጥጥር ውስጥ መሆኑን አሳይ። በተለይ የ23 ዓመት ወጣት በሰባት ወይም በስምንት አመት አንተን የምያንሱ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የምታስተምር ከሆነ ይህ እውነት ነበር። መምህራን የመማሪያ ክፍል አስተዳደር ክህሎት እንደሚያስፈልጋቸው ምንም ጥያቄ የለውም። ግን የግንኙነት ችሎታዎች፣ እና እነሱን ተግባራዊ ለማድረግ ጊዜ ያስፈልጋቸዋል፣ ይህም በደንብ ለሚሰራ የመማሪያ ክፍል ሁኔታዎችን ይፈጥራል ብዬ አምናለሁ። ጥሩ ግንኙነቶች የተማሪን ትምህርት ያሻሽላሉ። እና ምናልባት አስተማሪዎች በድርድር ላይ እንደ ተማሪዎቻቸው የሚያገኙትን ያህል ሊሆን ይችላል። Comments are closed.
|