ስለ እኔ
ለእኔ እና ለቤተሰቦቼ ከ 2013 ጀምሮ አርሊንግተን ቤታችን ሆኗል። በዮርክታውን የመጀመሪያ አመት ተማሪ የሆነ ወንድ ልጅ እና በኬንሞር የ7ኛ ክፍል ተማሪ የሆነች ሴት ልጅ አሉኝ። እኔና ባለቤቴ ያደግነው በሰሜን ቨርጂኒያ ሲሆን እኛ የቨርጂኒያ የሕዝብ K-12 ትምህርት ቤቶች እና ዩኒቨርሲቲዎች ኩሩ ምርቆች ነን። በክፍል ውስጥ የሁለተኛ ደረጃ እንግሊዘኛ እና ባዮሎጂ በማስተማር ጀምሬ፤ ስራዬ እስካሁን ድረስ ያሳለፍኩት በትምህርት ነው። ከዛም ለK-12 በድረገጽ ለመምህራን እና ተማሪዎች የሚቀርብ ትምህርት ለ PBS በማዘጋጀት አገልግያለሁ። በመጨረሻም ብሄራዊ የትምህርት ክፍላቸውን በመምራት ሰርቻለሁ። ጥሩ የትምህርት ፖሊሲን እና ፕሮግራሞችን እንዲገነዘቡ፣ እንዲደግፉ እና እንዲተገብሩ በመርዳት ከበርካታ የአካባቢ እና ብሔራዊ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ጋር ሰርቻለሁ። በአሁኑ ጊዜ ለ TED ለዕድሜ ልክ ትምህርት የኦንላይን ኮርሶችን በማዘጋጀት ላይ እየሰራሁ እገኛለሁ። ጥሩ TED Talk ለማየት ከፈለጉ፣ የ ይፋት ሱስኪንድን "በአጠራጣሪ ጊዜ፣ እንደ እናት አስብ" እመክራለሁ። እጅግ በጣም ሞኝ የሆነውን ማየት ከፈለጉ የ ጄምስ ቬቺን "ለአይፈለጌ መልዕክት ኢሜይል ሲመልሱ ይህ ነው የሚሆነው" የሚለውን ይመልከቱ። |